ክፍል 1፥ የጥናት መግቢያ1.1 ተፈላጊ ሶፍትዌሮችበመጀመሪያ ለጥናታችን የምንጠቀማቸውን ፕሮግራሞች እናያለን። ጥናቱን ለመከታተልና ምሳሌዎችን ለመሞከር፥ ከዚህ በታች የተመለከቱት ወይም ተመሳሳይ ፕሮግራሞች በቅድሚያ መዘጋጀት አለባቸው።
1.2 SVG ሥዕል ነደፋተለምዷዊ የመሣያ መሣሪያዎች እርሳስን፥ ቡርሽን፥ ቀለምንና ሌሎችን ይጨምራሉ። ሠዓሊዎች እነሱን በመጠቀም ወረቀት ላይ፥ ግድግዳ ላይ ወይም ጨርቅ ላይ ሥራቸውን ያሠፍራሉ። ሁሉም የእጅ ሥራ ነው። SVG ግን ከዚህ ተለምዷዊ አሠራር በብዙ መንገድ ይለያል። የሠዓሊው መሣሪያዎች በ«መመሪያ ቃል» ተተክተዋል። ወረቀቶቹና ሌሎችም በ«ሞኒተር ገጽ» እና «ማተሚያ» ተተክተዋል። 1.2.1 እርሳስና ወረቀትየSVG ሠዓሊ እርሳሱና ብሩሹ እንዲሁም ቀለሙ የSVG የ«ሥዕል-ቃላት» ናቸው። ወረቀቱ ወይም ሉኩ ደግሞ የሞኒተሩ ገጽ ነው። መቅረጽ የሚሻውን በእጁ ፈንታ በመመሪያ ይገልጻል። ተገቢውን መመሪያ አስከሰጠ ድረስ፥ እውን ሥራውን የሚሠራው ኮምፕዩተሩ ነው። የሥዕል-ቃላቱ ግልጽና የማያሻም ትርጉም ስላላቸው ባጠቃቀም ዘንድ ግር አይሉም። 1.2.2 የSVG ቃል አገባብና አጻጻፍየSVG የ«ሥዕል-ቃላት» አጻጻፍ፥ አገባብና አጠቃቀም በደንብ ላይ የተመሠረተ ነው። ደንቡ የሥዕል-ቃላቱን ሰዋሰውና መዝገበ-ቃላት እንዴት አድረገን መጠቀም እንዳለብን በግልጽ ያስቀምጣል። በዚህ ክፍል ራሳችንን ከሥዕል-ቃላቱ አጻጻፍ ጋራ እናስተዋውቃለን። ሁሉንም ለማወቅና ለመርመር የደንቡ ሰነድ እነሆ፦ SVG 1.1 መንደርደሪያ ይሆነን ዘንድ ከዚህ ምሳሌ እንነሳ።
በግራና በቀኝ (<>) ምልክት የታጠሩት የሥዕል-ቃላት ናቸው። የመጀመሪያው ከፋች ሥዕላዊ-ቃል ሲሆን የመጨረሻው ደግሞ ዘጊ ሥዕላዊ-ቃል ነው። የ«/» ምልክት ከፊቱ የጨመረው ዘጊው ቃል ነው። በXML ሕግ መሠረት ከፋች ቃል ያለዘጊ ወይም ዘጊ ቃል ያለከፋች አይፈቀድም። በሁለቱ መካከል የታቀፈው ንባብ (ተነባቢ ፊደል) (text) ነው። የ<text> ዓላማ ንባብን ወይም ፊደልን በሞኒተሩ ገጽ ላይ መሣል ሲሆን ፊደል መጻፍ ስንፈልግ የምንጠቀመው እሱን ነው። ወደ በኃላ የምንመለከታቸው አብረውት ሊሠሩ የሚችሉ ሌሎች አሉ። አንባቢው እንደሚያየው፥ የከፋቹ ቃል ሁለት ቁጥሮች ይጠቅሳል። አንደኛው የx-አክሰስ ነጥብ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የy-አክሰስ ነጥብ ነው። ንባቡ በሞኒተር ገጹ ላይ የት ጀመሮ መጻፍ እንዳለበት የሚያስታውቁት እነዚህ ናቸው። ሌላ ምሳሌ እንመልከት።
ይህ ሥዕላዊ-ቃል ክብ ይሠራል። በከፋቹ ቃል ያሉት የመጀመሪያዎቹ ሁለት ነጥቦች ማለትም cx እና cy የክቡን መኸከል ሲጠቁሙ r ደግሞ የክቡን ሬድየስ ይሰጣል። የመጨረሻው፥ ክቡ በጥቁር ቀለም መሞላት እንዳለበት ይናገራል። ይኸን ሥዕላዊ-ቃል በፊቱ ካየነው ምሳሌ ከሚለዩት መካከል አንዱ ይዘት አለማቀፉ ነው። ከዚህ የምንማረው፥ ሁሉም የሥዕል-ቃላት የግድ ይዘት ማቀፍ የለባቸውም። በተጨማሪ አንድ የሥዕል-ቃል ይዘት ከሌለው ራሱን በጭር መንገድ መግለጽ ይችላል። ለምሳሌ፦
ራሱን የቻለ ዘጊ-ቃል ከመስጠት ይልቅ፥ ከግራው የአንግል ብራኬት በፊት «/» በማስገባት ቃሉን ከፋችን ዘጊ ማድረግ ይቻላል። ስለሆነም፥ ይዘት የሌለው ሥዕላዊ-ቃል በዚህ አጭር መንገድ መጻፉ ስህተት አይሆንም። ተለምዷዊው አሠራር እሱ ነው። 1.2.3 የሥዕል አሠፋፈር (Coordinate System)ሥዕሎች የሚሣሉበት ቦታ ግልጽና በውል የታወቀ ነው። ቦታውን፥ ቢከፋም ቢበጅም፥ ከዚህ በኃላ «ሉክ» ብለን እንጠራዋለን። አንድ ሉክ የሞኒተሩን ገጽ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል እንዲሁም ከልክ በላይ ሊሸፍን ይችላል። እንደ ሠዓሊው ፍላጐት። በንድፈ-ሀሳብ ደረጃ፥ በSVG ረገድ የሉክ ስፋትና ቁመት ወሰን ላይኖረው ይችላል። የሉኩን ስፋትና ቁመት የመወሰኑ ኃላፊነት የሠዓሊው ነው። ሥዕሎቻችንን በሥነ ሥርዓት እንሥል ዘንድ የሉኩን ሁለመና መቆጣጠር እንችላለን። በመጀመሪያ የሉክን ስፋትና ቁመት እንዴት እንደምንለካ እንመልከት። የSVG ሉክ በx-አክሰስና በy-አክሰስ ላይ የተቀሰተ ነው። ሁለቱ አክሰሶች በስተግራ በኩል ከላይ ካለው ጠርዝ ይገናኛሉ። ሁለቱ የሚገናኙበት ጠርዝ በ(x,y) ረገድ (0,0) ተብሎ ይለካል። ይህ የመነሻ ነጥብ ነው። እኛ ከፈለግን ከዛ አንስትን ሌላ ቦታ ላይ መትከል እንችላለን። ወደፊት ይኸን የሚያደርግ ምሳሌ እናያለን። በx-አክሰስ ረገድ ከግራ ወደቀኝ ልኩ እየጨመረ ይሄዳል። በy-አክሰስ በኩል ከላይ ወደታች ልኩ እየጨመረ ይመጣል። ለምሳሌ የሚከተለው የሥዕል-ቃል መስመሩ ከየት ተጀምሮ የት ድረስ መሰመር እንዳለበት ይገልጻል። መነሻና መድረሻ ነጥቡ በx-አክሰስና በy-አክሰስ ረገድ መሰጠት አለበት። በሌላ መንገድ ቃሉን ብንገልጸው፦ ከ (10, 10) ጀምረህ እስከ (100,100) ድረስ መስመር ሥራ ይሆናል።
እንዲህ አይነት የቦታ አቀማመጥና አለካክ ዘይቤ «ካርትዣን ስልት» ተብሎ ይጠራል። ስሙ በስልቱ ፈልሳፊ «ከርትሰስ ዴካርትስ» የተሰየመ ነው። 1.2.4 የSVG ቃል አጠቃላይ መዋቅርየSVG ቃል መሠረታዊ መዋቅር አለው። ሁሉም አንድ አይነት መጀመሪያና መጨረሻ አለው። እናም ይኸን «ይመስላል»።
የመጀመሪያው ከፋች ቃል ሲሆን የመጨረሻው ደግሞ ዘጊ ቃል ነው። በሁለቱ መካከል ሌሎች የሥዕል-ቃላት ይገባሉ። ይህ መዋቅር ሕጋዊና ሁለመናዊ ነው። መጣስ ወይም መቀየር አይፈቀደም። በከፋቹ ቃል ውስጥ ስላለው ነገር ወደፊት እንመለስበታለን። ለጊዜው መሠረታዊው መዋቅር ላይ እናተኩር። ይህ መዋቅር ትርጉም የሚኖረው፥ በርግጥ ሥዕሎችን መሣል ስንጀምር ነው። ተግባራዊ መሳሌ እነሆ።
1.2.5 SVG በራሱ ፋይል ወይስ ከHTML ጋርs SVGን በሁለት መንገድ ማጠናቀር እንችላለን። ለብቻው ወይም ከHTML ጋራ። ሁለቱም ለይቅል የሆነ ጠቀሜታ አላቸው።
|
|||||||||||
contact@senamirmir.org
Copyright © 2002-2005 Senamirmir Project