XML Overview in Amharic









XML Overview
Introduction
HTML Overview
XML Overview












  


ሃቴማላ

፟ኤማላ፠ ምንድን ነው የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ፥ በመጀመሪያ ሃቴማላን (HyperText Markup Language) መመልከት ይጠይቃል።

ሃቴማላ፠ ፥ ሰነዶች በዌብ ገጽ ላይ እንዴት እንደሚቀመጡና መልካቸውስ ምን መምስል እንዳለበት መመሪያ መስጫ መንገድ ነው። የዌብ ገጽ ስፋት ፥ የፊደላት አይነትና ቀለም ፥ ያርስቶችና ያንቀጾች አቀማመጥ ፥ ካንድ ነጥብ ወደሌላ መስፈንጠሪያ መንገዶችንና የመሳሰሉትን ይገልጻል። ባጭሩ ፥ ሃቴማላ የገጽ መግለጫ ቋንቋ ነው። በሃቴማላ የታቀፉ ተነባቢ ነገሮች ፟ሃቴማላ ሰነድ፠ ወይም ፟ዌብ-ሰነድ፠ ብለን ልንጠቅሳቸው እንችላለን። ዌብ-ገጾች ተሳናድተው ቦታቸው እንዲሰፍሩ ከተደረገ በኋላ ፥ በመቃኛ-ፕሮግራም አማካኝነት ማንበብ ይቻላል።

ባጠቃላይ አንድ የሃቴማላ ሰነድ ሁለት ነገሮች ያቅፋል--ቃለ-ምልክቶችና ተነባቢ ይዘት። ቃለ-ምልክቶች ፥ ተነባቢው ነገር እንዴት መቀመጥ/መታይት/መጻፍ/መደርደር እንዳለበት ለመቃኛ-ፕሮግራም እዝ የሚሰጡ ሲሆን ተነባቢው ነገር ደግሞ ጽሑፍ ፥ ሥዕል ፥ ድምፅና ፥ ሌሎች ነገሮች ያካትታል። የሃቴማላ ቃል አጠቃቀም ሦስት ነገሮች ያሳትፋል፦

<ቃለ-ምልክት> ተነባቢ ነገሮች </ቃለ-ምልክት>

መቃኛ ፕሮግራም ይኸን ቃል ተርጉሞ ፥ በቃለ-ምልክት ውስጥ የታቀፈውን ተነባቢ ነገር ዌብ ገጹ ላይ ያስቀምጣል። የከፋችና ገጣሚ ቃለ-ምልክቶች ለመቃኛ-ፕሮግራሙ መመሪያ ናቸው--ትዕዛዝ እንዲሉ። ምስል 1.1 የሚያሳየው ይኸንኑ ነው። ከመመሪያው እንደምንረዳው ፥ ተነባቢው ነገር የገጹ መካከል ላይ መቀመጥ አለበት። መቃኛ-ፕሮግራሙ የዌብ ገጹን ስፋት ለክቶ ፥ ተነባቢውን ቃል መካከል ላይ ይጽፋል።

  ምስል 1.1
 
   
  • <center>፦ እንደዚህ አይነት ፟ካፋች ቃለ-ምልክት፠ በእንግሊዘኛ open/start tag ተብሎ ይጠራል።
  • </center>፦ እንደዚህ አይነት ፟ገጣሚ ቃለ-ምልክት፠ በእንግሊዘኛ close/end tag ተብሎ ይጠቀሳል። ገጣሚ የሆነው በ፟/፠ ምልክት ነው።

ምሳሌያችን ፟በርክበ ቃል፠ (syntax) አንጻር አቋቋሙ ስህተት ባይኖረውም ፥ ሙሉ የሃቴማላ ሰነድ ለመሆን ቢያንስ ሁለት ጉድለቶች አሉት። ቀጥለን የተሟላ የሃቴማላ ሰነድ እንመለከታለን።

  ምስል 1.2
 
<html>
<body>
    <center>
      Erta-Ale, Voice of the Afar!
    </center>
</body>
</html>

   

እያንዳንዱ ቃለ-ምልክት ከፋችና ገጣሚ ወገን አለው። የ<html> ቃለ-ምልክት የሰነዱ አይነት ምን እንደሆነ ይናገራል። የ<body> ቃለ-ምልክት ደግሞ የዌብ ገጹ ሰውንት የት ጀምሮ ፥ የት እንደሚጨርስ ይገልጻል። በመጨረሻ ፥ የ<center> ቃለ-ምልክት በውስጡ የታቀፈው ተነባቢ ነገር በጎን የገጹ መካከል ላይ መስፈር አለበት ይላል።

ሠንጠረዥ

መረጃዎች/ዴታዎች አጠናቅረን ከምናቀርብበት መንገድ አንዱ ሠንጠረዥ ነው። የሠንጠረዥ አካል በረድፍና ባምድ የተሸነሸነ ሆኖ አርእስቶች ካሉት የመጀመሪያው ረድፍ ወይም ዓምድ ላይ ይሠፍራሉ። የሚከተለውን ምሳሌ እንመልከት።

  ምስል 1.3
 
Rivers          Length 
------------   ---------------
Nile            6696 km
Awash           700 km
Tekeze          752 km
Omo             644 km
   

ይህ ሠጠንረዥ ከነአርእስቱ ፥ አምስት ረደፍ ሲኖረው በቁሙ ደግሞ ሁለት አምድ አለው። ባለ ፟5በ2፠ እንዲሉ። አንባቢዎች ፥ የሠንጠረዡን አርእስት ተመልክተን እያንዳንዱ ዓምድ ምን ኢይነት መረጃ እንደሚያቅፍ መለየት እንችላለን። በሌላ አነጋገር ፥ አርእስቶቹ የሠንጠረዡን ምንና ማንነት ይነግሩናል። ይህ እውነት የሚሆነው ግን አርእስቶች ለተሰጡት ሠንጠረዥ ብቻ ነው። ሠንጠረዡን ዌብ ገጽ ላይ ማስቀመጥ በምንችልበት መንገድ ብናሰናዳ ፥ ውጤቱ ይኸን ይመስላል።

ምስል 1.4

1.  <html>
2.  <body>
3.    <table>	
4.      <tr>  <td> Rivers </td>    <td> Length  </td>  </tr>
5.      <tr>  <td> Nile   </td>    <td> 6696km  </td>  </tr>
6.      <tr>  <td> Awash  </td>    <td> 700km   </td>  </tr>
7.      <tr>  <td> Tekeze </td>    <td> 752km   </td>  </tr>
8.      <tr>  <td> Omo    </td>    <td> 644km   </td>  </tr>
9.    </table>
10. </body>
11. </html>

 

በግራ በኩል ያሉት ተራ ቁጥሮች የንባቡ ክፍሎች አይደሉም። የተጨመሩት ለመወያየት ይረዱ ዘንድ። ከቁጥር 1 እስከ 11 ድረስ የተጻፉት ነገሮች ባንድ የዌብ-ሰነድ ይወካላሉ። መጨመር ያለባቸው አንዳንድ ነገሮች አሉ። ብንተዋቸው ግን በደል አያስከትሉም።

ይህ ሰነድ አንድ ሠንጠረዥ አለው። ከቁጥር 3 ጀምሮ እስከ ቁጥር 9 ያለው። ይህ በ<table> (ከፋች ቃለ-ምልክት) እና በ</table> (ገጣሚ ቃለ-ምልክት) ይለያል። አንባቢው እንደሚረዳው ፥ አንድ ሠንጠረዥ ያንድ ወይም የበለጠ ረድፎች ውጤት ነው። እያንዳንዱ ረድፍ በ<tr> ቃለ-ምልክት ተክፍቶ በ</tr> ቃለ-ምልክት ተገጥሟል። እያንዳንዱ ረድፍ ደግሞ ያንድ ወይም የበለጠ ዓምዶች ውጤት ነው። በተራው ፥ እያንዳንዱ ዓምድ በ<td> ቃለ-ምልክት ተከፍቶ በ</td> ቃለ-ምልክት ተገጥሟል።

እያንዳንዱ አምድ ለምን እንደሚቆም ለመረዳት ይዘቱን እናነባለን። መቃኛ ፕሮግራም ሠንዘረዡን ዌብ-ገጽ ላይ ሲቀዝፍ ፥ በወል የሚመለከተው ሠንጠረዡ በሁለት ዓምድ መከፈሉን ነው--በ<td> ቃለ-ምልክት አማካኝነት። በውስጡ ስላለው ይዘት ግን ማወቅ የሚችልብት መንገድ የለውም። ቃለ-ምልክቶቹ የሚነገሩት ፥ ተነባቢ አካሎች እንዴት ዌብ-ገጹ ላይ መሥፈር እንዳለባቸው ብቻ ነው። ስለዚህ ፥ የ<td> ቃለ-ምልክት ፥ ዓምድ ለመገንባት እንጂ ፥ በዓምዱ ውስጥ ስላለው ይዘት የሚነግረን ነገር የለም።

ባጠቃላይ ፥ የሃቴማላ ቃለ-ምልክቶች አብይ ዓላማ ፥ አንድ ተነባቢ አካል የት እንዲሁም እንዴት መታየት እንዳለበት መግለጽ ብቻ ነው። ይዘቱ ቁጥር ይሁን ወይም ስድ-ንባብ ግድ የላቸውም። ከዚህ ተነስተን ፥ የሃቴማላ ተግባር ተነባቢ አካሎች መግለጫ መንገድ ወይም ቋንቋ ነው ብለን መደምደም እንችላለን።

በኢንተርነት ላይ መረጃ ለመቀያየር ፥ ለመቀባበል ፥ ብሎም ለመረዳትና ተገቢ እርምጃ ለመውሰድ ፥ ስለመረጃዎች ምንና ማንነት ማወቅ ተፈላጊ ነው። በመሠረቱ መረጃ መቀባበል ወይም መለዋወጥ አዲስ ነገር ነው ለማለት ሳይሆን በኢንተርነት ደረጃ ፥ በብዙኋኑ ተቀባይነት ባለው መንገድ ማድረጉ ግን ዘላቂና አያሌ ጥቅሞች አሉት።

ኤማላ፠ (XML) በመረጃዎች ወይም ባጠቃላይ በይዘቶች አቀራረባና ማንነት መካከል ያለውን ልዩነት በግልጽ ያከብራል። ዓላማው ፥ የመረጃዎችንና ወይም ይዘቶችን ምንና ማንነት መደንገግና መግለጽ ነው። በሚቀጥለው ክፍል ኤማላን እንመለከታለን።



...
smirmir@senamirmir.org
©Senamirmir Project, 2001