-
ኤማላ (XML) ለመጠቀም ምን ማድረግ አለብኝ?
እንደጠያቂው። የኤማላ ሰነድ ለማዘጋጀት ከሆነ ፥ ወደፊት
እንደርስበታለን። ለአቅመ-ሥራ የደረሰ የኢማላ ሰነድ ዌብ
ገጽ ላይ ለሙከራ ያህል ለማየት ከሆነ ፥ አንዳንድ ሥራዎች
አሉ። እንዚህን ሥራዎች ዌብ ላይ ለመመልከት የግድ መቃኛ
ፕሮግራም ይጠይቃል።
ባሁኑ ወቅት ፥ መቃኛ ፕሮግራሞች ኤማላን ይደግፉ ዘንድ
ከፍተኛ ሥራዎች እየተካሄዱ ናቸው። ስለዚህ ፥ አሁኑኑ
ከመቃኛ ፕሮግራሞች ብዙ መጠበቅ ያዳግታል። አብዛኛዎቹ ፥
በሲ/ኤስ/ኤስ (CSS-Cascading Style Sheet)
የተቀረጹ የኤማላን ሰነዶች በመልካም ሁኔታ ዌብ ገጽ ላይ
ማሳየት ይችላሉ። ሞዚላ (Mozilla) ፥ አይ/ኢ
(Internet Explorer) እና ኦፕራ (Opera)
ይገኙበታል። ለሰፊ ማብራሪያ የነዚህን ፕሮግራሞች ገጽ
ይምልከቱ።
ለናሙና የሚያገለግሉ ጥቂት ሥራዎች አሉ። እነሱን
በሞመከር ራስን ከኤማላ ሁኔታ ጋር ማለማመድ ይቻላል።
እንደምሳሌ ከሚቀርቡት መካከል ሁለቱ የሚከተሉት ናቸው።
የራስን ኤማላ ለማዘጋጀት ውጥን ካለ ፥
ሰነድ ደራስያን
እና
የፕሮግራም ጸሐፊዎችን
ክፍሎች ይመልከቱ።
-
በሃቴማላ (HTML) ምትክ ለምን ኤማላን እመርጣለሁ?
ሰነድ አዘጋጆች/ደራሲዎች የራሳቸውን ገላጭ/መታወቂያ
ቋንቋ ፍጥረው መጠቀም ይችላሉ። የግድ ራሳቸውን
የሃቴማላ ቁራኛ ማድረግ አይኖርባቸውም። ሸንሽነው ፥
መዋቅር ዘርግተው ፥ መታወቂያ ስሞች አድለው ፥
ሰነዶችን ትርጉማዊ ብሎም ተባባሪ ማድረግ ፥
አመልካችነቱ ፥ ምን ያህል በሰነዳቸው ላይ ከፍተኛ
ቁጥጥር እንደሰጣቸው ነው። ይህ በሃቴማላ በኩል
የማይሸተትና የማይቀመስ መና ነው።
በኤማላ የተዘጋጁ ሰነዶች ራስ ገላጭ ስለሆኑ ፥
ፕሮግራሞች ያለሰው ጣልቃ-ገብነት መርምረው
ሁለንተናቸውን መረዳት አይሳናቸውም። እንደተፈለገ ፥
ይዞቶችን ከመታወቂያ ስማቸው ለይተው ፥ አያሌ
ተግባሮች መፈጸም ይችላሉ። ዴታ ማጠራቀሚያ ውስጥ
በሥነ ሥርዓት መክተት ፥ ለዌብ ገጽ እይታ ማመቻቸት ፥
ለንግድ ሥረዎች መልክት ማመላለስና ሌሎች የሚታሰቡ
ጨምሮ።
የኤማላ ሰነዶችን በልዩ ልዩ መልክ ለዌብ ገጽ ማቅረብ
የሰጠ ነው። ለዚህ ሂደት ኤክስ/ኤስ/ኤል (XSL)
እንደድልድይ ሆኖ ሲያገለግል ፥ ሲ/ኤስ/ኤስ (CSS)
ደግሞ የዌብ ገጹን መልክ ለመቅርጽ ወደር የሌለው
ማለፊያ ነው።
ኤስ/ጂ/ኤም/ኤል (SGML) ባገልግሎቱ ከሁሉ የላቀ ፥
ለብዙ ዓመታት በሥራ የዋለ ቢሆንም ቅሉ ፥ ወደ
ኢንተርነት ለመሳብ ጫናው ከባድ ነው። በተለይ ላጠቃቀም
አለመመቸቱ። ይሁን እንጂ ኤስ/ጂ/ኤም/ኤልን ምስጋና
ልነነሳ አይገባም ፥ ኤማላን እስከሰጠ። በኤማላ በኩል ፥
ሁሉንም ባይሆን ፥ መሠረታዊ የኤስ/ጂ/ኤም/ኤልን ኃይል
እናገኛለን። በተፈጥሮው የተነሳ ፥ ሃቴማላ ለዚህ ተልዕኮ
ብቃት የለውም።
ኤማላ በኢንተርነት ደንበር የተገደበ አይደለም። ራሱን
ለፈለጉት ሁሉ ይለግሳል ፤ የትኛውንም ኃይሉን ሳይቀንስ።
-
የኤማላ መቃኛ ፕሮግራም የት አገኛለሁ?
ኤማላን በሚመለከት የጎላ ጥረት እያሳዩ ያሉ
መቃኛ ፕሮግራሞች ስም ዝርዝር ሞዚላ (ኔትስኬፕ
ናቭጌተር) ፥ አይ/ኢና ፥ ኦፕራን ይጨምራል።
እነዚህ መቃኛ ፕሮግራሞች ኤማላን እስከምን
ድረስ ይቀበላሉ?
በመለስተኛ ደረጃ ቢባል ፥ ድጋፋቸውን
ለማንኳሰስ እንዳይደለ አንባቢው ይረዳ።
ኤማላ ፥ አሁንም አዲስ በመሆኑ ፥ ከሞላ
ጐደል አብዛኛዎቹ ሥራዎች በሂደት ላይ
ናቸው። ሙከራዎችን ጨምሮ።
ለአቅመ-ሥራ ሊደርሱ የሚችሉ የኤላማ ሰነዶች
አይነት ከመጠን በላይ ስለሆነ ፥ አንድ
የመቃኛ ፕሮግራም ሁሉን አካቶ ይደግፋል
ለማለት ይከብዳል። ቢታሰብም ፥ ጊዜ
እንደሚፈጅ አንዘንጋ ፥ ምኞታችን እንኳን ቢሆን።
ጎልተው የሚታዩ ፥ ሰፊ ስርጭት ያላቸው
የመቃኛ ፕሮግራሞች ዝርዝር ቀጥሎ
ቀርቧል።
-
አይ/ኢ (Internet Explorer)
በተወሰነ ደረጃ ኤማላን ይቀበላል።
የማይክሮሶፍትን ገጽ ላዲስ ነገሮች መመልከቱ አይከፋም።
-
የሞዚላ መቃኛ ፕሮግራም ወይም በሌላኛው
መልኩ ኔትስኬፕ ናቭጌተር 6.1 ፥ የኤማላን
ሰነዶች ዌብ ገጽ ላይ ማቅረብ ይችላል ፤
በሲ/ኤስ/ኤስ (Cascading Style Sheet)
እስከተቀረጹ ድረስ። ሲ/ኤስ/ኤስ የገጾች
መልክ መፍጠሪያ ቋንቋ ነው። ለተጨማሪ ማብራሪያ
የሞዚላን ገጽ
ይመልከቱ።
-
ከሁሉም በላይ ኤማላን ለመደገፍ ቆርጠው ከተነሱ
ቡድኖች መካከል አንዱ የሳይተክ (CITEC)
ቡድን ነው። ከሞዚላ ሰዎች ጋር በመተባበር ፥
የተሟላ ግላጋሎት የሚሰጥ የመቃኛ ፕሮግራም
ለመገንባት በሥራ ላይ ናቸው። ለዚህ ይረዳቸው
ዘንድ ዌብ ገጽ አቋቁመዋል። እሱም
ዳክዚላ
ነው።
-
በፍጥነቱ ዝና ያተረፈ የመቃኛ ፕሮግራም
ቢኖር ኦፕራ (Opera) ነው። እንደ
ሞዚላ ሁሉ ፥ የኤማላን ሰነዶች
ከሲ/ኤስ/ኤስ ጋር ዌብ ገጽ ላይ ማሳየት
ይችላል። ኦፕራ ሁለት አይነት ስርጭት
አለው። የነጻው ከማስታወቂያ ጋር ሲመጣ
የባለግዢው ግን ንጹህና ጣጣ የለበትም።
ለበለጠ ማብራሪያ የሚከተለውን ገጽ
ይመልከቱ።
ኦፕራና ኤማላ።
-
ከኤስ/ጂ/ኤም/ኤል ወይም ከሃቴማላ ወደ
ኤማላ መሸጋገር አለብኝ?
ኤስ/ጂ/ኤም/ኤል በራሱ መቀጠሉ አይቀርም።
ሃቴማላም ቢሆን እንደዚሁ። በተግባር የዋሉ
ሥራዎችን መቀየሩ ጥቅሙ ካለመዘነ በስተቀር
ባዛው መቆየቱ አይካፋም። ምናልባት የሃቴማላን
ሰነዶች ወደ ኤክስ/ኤች/ቲ/ኤም/ኤል
(XHTML) መለወጡ ጥቅም ይኖረዋል።
ለዚህ ዋናው ምክንያት ፥ ኤክስ/ኤች/ቲ/ኤም/ኤል
(XHTML) በህጎቹ ጥብቅና አስከባሪ ነው።