XML Frequently Asked Question in Amharic
|
|
መግቢያኤማላ ፥ ከእንግሊዘኛው (Extensible Markup Language) ስም የተወሰደ ቃል ነው። ሌላኛው አማራጭ ኤክስ/ኤም/ኤል (XML) ነበረ። ነገር ግን ላጻጻፍ አመቺ አይደለም ፤ ስለዚህ ኤማላ። ይህ ስለኤማላ ተደጋጋሚ መጠይቅና ምላሽ (Frequently Asked Questions) ዝርዝር ነው። የሚያተኩረው ኤማላ ላይ ብቻ ስለሆነ ፥ ያንባቢው ጥያቄ ስለሃቴማላ (HTML) ፥ ስለስክሪፕት ቋንቋ ፥ ስለፕሮግራም መጻፊያ ቋንቋ ወይም ስለሌላ ከሆነ ፥ ይህ ቦታ ትክክለኛ አይደለም። ይህ ተደጋጋሚ መጠይቅና ምላሽ (ተመም) ፥ ፕሮግራም ጸሐፊዎች ፥ ኤማላ ተጠቃሚዎች እንዲሁም ፍላጎት ያላቸውን በሙሉ በምንጭነት ይረዳል የሚል እምነት አለ። ለማሳሰብ ያህል ፥ ይህ ሥራ የኤማላ (XML) ደንብ አይደለም። ምሥጋናየሚከተሉት ሰዎች ለዚህ ሥራ አስተዋጽኦ አድረገዋል። ቴሪ አለን (Terry Allen) ፥ ታም ቦርግማን (Tom Borgman) ፥ ቲም ብሬይ (Tim Bray) ፥ ሮቢን ከቨር (Robin Cover) ፥ ባብ ዱቻርም (Bob DuCharme) ፥ ክርስቶፈር ማደን (Christopher Maden) ፥ ኤቭ ሜለር (Eve Maler) ፥ መኮቶ ሙራታ (Makoto Murata) ፥ ፒተር ሙሬይ-ረስት (Peter Murray-Rust) ፥ ሊያም ኩይን (Liam Quin) ፥ ማይክል እስፐርበርግ-መኩይን (Michael Sperberg-McQueen) ፥ ጆል ዌበር (Joel Weber) ፥ እና ብዙ የSIG አባላት እንዲሁም የዚህ ሰነድ አንባብያን ባለም-አቀፍ ደረጃ። እርማት ፥ ተጨማሪ ነገር ፥ ወይም ጥያቄ ስለሰነዱ ካሎት ላዘጋጁ ይላኩ። ጥያቄው ለየት ካለ ፥ ለተገቢው የዜና-መድረክ ያቀርቡ ዘንድ ማሳሰቢያው እነሆ። በቅርብ የተደረጉ ለውጦችየሰነዱ ሰአደ (DTD) ከDocBook SGML ወደ QAML XML ተቀይሯል። ቅንብርይህ ተመም (FAQ)ባራት ክፍሎች ይከፈላል። ሀ) አጠቃላይ ለ) ኤማላ ተጠቃሚዎች ሐ) ኤማላ ደራሲያ እንዲሁም መ)ሶፍትዌር ገንቢዎች። በዚህ ተመም ስህተቶች ካሉ ወይም ትችት ካሎት ለተመም ጠባቂ በሚከተለው አድራሻ pflynn@ucc.ie ይጻፉ። ስለኤማላ (XML) ደንብ አስተያየት ካሎት የW3C ገጽ ይጎብኙ። ስርጭትይህ ሰነድ በተለያየ ቅርጽ ይሰራጫል። ዝርዝሩ እነሆ።
ይህ ሰነድ በተለያዩ ቋንቋዎች ተተርጉሟል።
|
|
smirmir@senamirmir.org ©Senamirmir Project, 2001 |